Image

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

Benishangul Gumuz Regional State Health Bureau

መቀንጨር በትውልድ ላይ የሚያደርሰውን ዘርፈ ብዙ ችግር ለመቅረፍ የሚመለከታቸዉ ሴክተር መ/ቤቶች በትኩረት መሥራት እንዳለባቸዉ ተመላከተ።

መቀንጨር በትውልድ ላይ የሚያደርሰውን ዘርፈ ብዙ ችግር ለመቅረፍ የሚመለከታቸዉ ሴክተር መ/ቤቶች በትኩረት መሥራት እንዳለባቸዉ ተመላከተ። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የምግብ ሥርዓት እና ሥርዓተ ምግብ ፕሮግራም ተግባሪ መ/ቤቶች በምግብ ሥርዓት እና ሥርዓተ ምግብ ም/ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ ዙሪያ መክረዋል ። በሀገር አቀፍ ደረጃ በ2022 መቀንጨርን ዜሮ ለማድረግ ብሄራዊ የሥርዓተ ምግብ ፕሮግራም ተቀርፆ በክልሎች የሥርዓተ ምግብ አብይ ኮሚቴ እና ቴክኒክ ኮሚቴ ተቋቋሞ በዘርፌ ብዙ ተግባራት ሲከናወኑ እንደነበረ ይታወቃል ። እነዚህን ሥራዎች አጠናክሮ ለማስቀጠል ደንብ ወጦለት በምክር ቤት ደረጃ መቋቋም ስለአለበት በረቂቅ የመቋቋሚያ ደንብ ላይ በጋራ ለመወያየት የሚያስችል የትዉዉቅ መድረክ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተካሄዷል ። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታሁን አብዲሳ በዉይይት ወቅት ከምግብ ሥርዓት እና የሥርዓተ ምግብ ሥራዎችን ሊያሳልጡ የሚችሉ የተለያዩ አግባብነት ያላቸው አሰራሮችን ዘርግተን እንደ ክልል መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል ይገባል። ከስርዓተ ምግብ መዛባት ጋር በተያያዘ በሰዎች ላይ የሚገጥሙ ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ለመፍታት ዘርፉ የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ የሚጠይቅ በመሆኑና በባለቤትነት የሚያስተባብርና የሚፈፅም አካል የሚጠይቅ በመሆኑ ምክር ቤቱን ማቋቋም እንዳስፈለገ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ገልፀው የመቀንጨር ችግሮች በትውልድ ላይ የሚያደርሰውን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጫና ለመቅረፍ የተዘጋጀው የም/ቤት ማቋቋሚያ ደንብ በቅርብ ጊዜ ዉስጥ ፀድቆ ወደ ሥራ እንዳገባ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መሥራት እንዳለባቸው አሳስበዋል ። አምራች የሆነ በዕዉቀት የበመለፀገ ዜጋ ለማፍራት መቀንጨርን ለማስቀረት በሚችሉ ጉዳዮች ላይ በትኩረት ሊሰራበት የሚገባ ጉዳይ ነው ያሉት አቶ ጌታሁን ችግሩን ለመቅረፍ የወጡ የስርዓተ ምግብ ፍኖተ ካርታ ፣ እስትራቴጂዎች እና የሰቆጣ ቃልኪዳንን ለመፈፀም አግባብነት ያላቸውን መዋቅር፣ አደረጃጀት ፣ በጀትና የሰው ሀይል በሁሉም ደረጃ እንዲኖር በማድረግ ምክርቤቱ በቀጣይ በትኩረት ይሰራልም ብለዋል። በመድረኩ የምግብ ሥርዓትና ስርዓተ - ምግብ ምክር ቤት ለማቋቋም የተዘጋጀው ረቂቅ ደንብ ቀርቦ ዉይይት ተደርጎበታል ። በዉይይት መድረኩ ላይ የክልሉ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ዶ/ር ተመስገን ዲሳሳ፣ የአሶሳ ዩንቨርሲቲ ፕረዘዳንት ዶ/ር ከማል ጨምሮ ከፍተኛ የክልሉ አመራሮች፣ባለሙያዎች እና በሥርዓተ ምግብ ፕሮግራም ላይ የሚሰሩ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።