Image

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

Benishangul Gumuz Regional State Health Bureau

በክልሉ ለሚገኙ 4 ወረዳዎች በSDH ፕሮጀክት ሞተር ተከፋፈለ

Wacho Wabulcho, [8/19/2022 9:18 AM] (13/12/2014 ዓ.ም) የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራምን በማሻሻል የእናቶችና የህጻናት ሞት ለመቀነስ የሚያስችል በቀጣይ 15 ዓመት ተግባራዊ የሚደረገውን የጤና ኤክስቴንሽን ማሻሻያ ፍኖተ ካርታ መሰረት የክልሉ የ5 አመት የድርጊት መረሀ ግብር ተዘጋጅቶ እየተሰራ መሆኑን የቡኒሻጉል ጉሙዝ ክልል መንግሰት ጤና ቢሮ ገለጸ፡፡ ከ1998 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ በመደረግ ላይ የሚገኘው የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም የማህበረሰቡን የጤና አገልግሎት ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ አንጻር ትልቅ ሚና የነበረው ቢሆንም በፕሮግራሙ ላይ በነበሩ ውስንነቶች በተለይ በጤና ኬላ ደረጃ የሚሰጡ አገልግሎቶች የተሟሉ አለመሆን ፣የሙያ ስብጥሮችን ያማከለ የሰው ሀይል አስተዳደርና ልማት ውስንነቶች እንዲሁም የግብአት አቅርቦት እና አስተዳደር ውስነንቶች መኖራቸውን በተደረገው ጥናት በመረጋገጡ አዲስ የጤና ኤክስቴሽን ፍኖተ ካርታ ማዘጋጀት አስፈልጓል። በቤኒሻጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ የጤና ኤክስቴሽንና የመሰረታዊ ጤና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክትር አቶ ክብሩ ሰባኔ በተዘጋጀዉ ፍኖተ ካርታ መስረት ወደ ስራ ለመግባት በ410 የጤና ኬላዎችን ደረጃ የመለየት ስራዎች ተሰርተዉ 74 የጤና ኬላዎች ወህድ፤61 ቀቤለዎች፤አጠቃላይጤና ኬላዎችና 275 ጤና ኬላዎች በመሰረታዊ የጤና ኬላነት በከፋፈላቸዉን ገልጸዋል፡፡ በተለዩ የጤና ኬላዎች ደረጃ መሰረት ወደ ትግበራ ስራ ለመግባት በየደረጃዉ የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ግንዛቤ ማዳበር አስፈላጊ በመሆኑ በየደረጀዉ ለሚገኙ የአመራር አካላትና ለባለድርሻ አካላት በክልል ፤በዞንና በወረዳ ደረጃ የተለያዩ የንቅናቀ መድረኮች መዘጋጀታቸዉን ነዉ አቶ ክብር የገለጹት፡፡ በአዲሱ ፍኖተ ካርታም አገልግሎቶች ላይ ለውጦች መኖራቸውን የጠቀሱት አቶ ክብሩ በተለይ ቤት ለቤት የማህበረሰብ ጉብኝት፣በትምህርት ቤትና በጤና ኬላ ላይ በመንቀሳቀሱ ባለሙያዎች አገልግሎት ይሰጣሉ።በዚህ አጠቃላይ በጤና ኬላ ደረጃም ከላብራቶሪ በስተቀር የተለያዩ የጤና አገልግሎቶች በፍኖተ ካርታው እንደተካተቱም ተደርጓል ብሏል። በዚሁ ፍኖተ ካርታ መስረት በሀገር አቀፍ ደረጃ በ14 ወረዳዎች የተጀመረ ሲሆን በቤኒሻጉል ጉሙዝ ክልል መንግሰት በባምባሲ ወረዳ መንደር 43 ጤና ኬላ በፓይለት የተጀመረ ስለሆነ ለፕሮግራሙ መሳካት የሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት የበኩላቸዉን ድርሻ መወጣ እንዳለባቸዉ አቶ ክብሩ ጥሪ አቀርበዋል፡፡ Wacho Wabulcho, [8/19/2022 9:23 AM] [ Photo ] Wacho Wabulcho, [8/19/2022 9:23 AM] [ Photo ] Wacho Wabulcho, [8/19/2022 9:23 AM] [ Photo ] Wacho Wabulcho, [8/19/2022 6:07 PM] ( 13/12/2014 ዓ.ም )የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ በአዉሮፓ ህብረት የገንዘብ ድጋፍ ከ3.2 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገዙ 22,ሞተሮችን ለፕሮጀክቱ ወረዳዎች አከፋፈለ። በአዉሮፓ ህብረት የገንዘብ ድጋፍ ማህበራዊ ተግዳሮቶች በመቅረፍ ለጤና መሻሻልና ለሥርዓተ ፆታ እኩልነት /SDH/ ፕሮጀክት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተመረጡ አራት ወረዳዎች በጤና ጣቢያ ጤና ኬላ ትስሰር ፣ በቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት ፣ በእናቶች ጤና፣በሥርዐተ ምግብ ፕሮገራም እና የጤና ተቋማት የዉሀ አቀርቦትን በማሻሻል በኩል ዘርፌ ብዙ ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛል ። እነዚህን የተጀመሩ ተግባራት አጠናክሮ ለማስቀጠል እና የትራንስፖርት እጥረት በጤናው ሥራ ላይ የሚያስከትለውን ጫና ለመቅረፍ ታስቦ በ4 ወረዳዎች ለሚገኙ 11 የጤና አጠባበቅ ጣቢያቸው አገልግሎት የሚዉሉ 22 የሞተር ሳይክሎች ተገዝተው እንዲከፋፈሉ መደረጉን የአዉሮፓ ህብረት ቴክኒካል አማካሪ ዶ/ር ሽባባዉ ታደሴ ገልፀዋል ። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ ፍቃዱ ረጋሳ ለፕሮጀክት ወረዳዎች የቁልፍ ርክክብ ካደረጉ በኋላ በዛሬዉ ዕለት የተደረጉ የሞተር ሳይክሎች እገዛ የፕሮጀክቱን ሥራዎች ከማሳለጥ በተጨማሪ ሌሎች የጤና ፕሮግራሞችን ለመደገፍ የሚያግዝ መሆኑን ገልፀው ለተደረገው እገዛ ለአውሮፓ ህብረት ላቅ ያለ ምስጋና አቀርበዋል ። በፕሮጀክቱ ዛሬ ርክክብ ከተደረጉ የሞተር ሳይክሎች በተጨማሪ ለፕሮጀክቱ ሥራ አገልግሎት የሚዉሉ የ3 መኪናዎች እና ቀሪ 7 ሞተሮች ግዥም በሂደት ላይ እንደሚገኝ የገለፁት የቢሮ ሀላፊ እነዚህ ተሽከርካሪዎች ለታለመላቸዉ ዓላማ ብቻ መዋል እንደአለባቸዉ አሳስበዋል ። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ማህበራዊ ተግዳሮቶች በመቅረፍ ለጤና መሻሻልና ለሥርዓተ ፆታ እኩልነት /SDH/ ፕሮጀክት ሥራ አስከያጅ አቶ አብዱልሙኒየም አልበሽር በበኩላቸው ፕሮጀክቱ ዛሬ ካከፋፈላቸው እና በግዥ ሂደት ላይ ከሚገኙ ተሸከርካሪዎች በተጨማሪ በጤና ተቋማት መካከል የተናበበ እና ጥራት ያለው የጤና መረጃ ሥርዓት ለመዘርጋት የIT ቁሳቁሶችን የማሟላት ሥራዎች እንደሚሰራ ገልጸዋል ። የህብረተሰቡን የንቃተ ጤና በማዳበር ህብረተሰቡ ለጤናው ሥራዎች መሳካት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ለማድረግ የሚኒ ሚዲያ ቁሳቁሶች የመግዛት እና ለፕሮጀክቱ ወረዳዎች የማከፋፈል ተግባራት በቀጣይ እንደሚከናወን አቶ አብዱልሙኒየም ተናግረዋል ። የየወረዳዎቹ ተወካዮች በበኩላቸው የተደረገው የተሽከርካሪ እገዛ ቀልጣፋና ጥራት ያለው የጤና ሥራ ለመስራት እንደሚረዳቸው ገልጸዋል ። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ መንግስት ክልል ጤና ቢሮ