Image

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

Benishangul Gumuz Regional State Health Bureau

የጤና ኤክስቴንሽን ማሻሻያ ፍኖተ ካርታ

(13/12/2014 ዓ.ም) የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራምን በማሻሻል የእናቶችና የህጻናት ሞት ለመቀነስ የሚያስችል በቀጣይ 15 ዓመት ተግባራዊ የሚደረገውን የጤና ኤክስቴንሽን ማሻሻያ ፍኖተ ካርታ መሰረት የክልሉ የ5 አመት የድርጊት መረሀ ግብር ተዘጋጅቶ እየተሰራ መሆኑን የቡኒሻጉል ጉሙዝ ክልል መንግሰት ጤና ቢሮ ገለጸ፡፡ ከ1998 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ በመደረግ ላይ የሚገኘው የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም የማህበረሰቡን የጤና አገልግሎት ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ አንጻር ትልቅ ሚና የነበረው ቢሆንም በፕሮግራሙ ላይ በነበሩ ውስንነቶች በተለይ በጤና ኬላ ደረጃ የሚሰጡ አገልግሎቶች የተሟሉ አለመሆን ፣የሙያ ስብጥሮችን ያማከለ የሰው ሀይል አስተዳደርና ልማት ውስንነቶች እንዲሁም የግብአት አቅርቦት እና አስተዳደር ውስነንቶች መኖራቸውን በተደረገው ጥናት በመረጋገጡ አዲስ የጤና ኤክስቴሽን ፍኖተ ካርታ ማዘጋጀት አስፈልጓል። በቤኒሻጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ የጤና ኤክስቴሽንና የመሰረታዊ ጤና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክትር አቶ ክብሩ ሰባኔ በተዘጋጀዉ ፍኖተ ካርታ መስረት ወደ ስራ ለመግባት በ210 የጤና ኬላዎችን ደረጃ የመለየት ስራዎች ተሰርተዉ 74 የጤና ኬላዎች ወህድ፤61 ቀቤለዎች፤አጠቃላይጤና ኬላዎችና 275 ጤና ኬላዎች በመሰረታዊ የጤና ኬላነት በከፋፈላቸዉን ገልጸዋል፡፡ በተለዩ የጤና ኬላዎች ደረጃ መሰረት ወደ ትግበራ ስራ ለመግባት በየደረጃዉ የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ግንዛቤ ማዳበር አስፈላጊ በመሆኑ በየደረጀዉ ለሚገኙ የአመራር አካላትና ለባለድርሻ አካላት በክልል ፤በዞንና በወረዳ ደረጃ የተለያዩ የንቅናቀ መድረኮች መዘጋጀታቸዉን ነዉ አቶ ክብር የገለጹት፡፡ በአዲሱ ፍኖተ ካርታም አገልግሎቶች ላይ ለውጦች መኖራቸውን የጠቀሱት አቶ ክብሩ በተለይ ቤት ለቤት የማህበረሰብ ጉብኝት፣በትምህርት ቤትና በጤና ኬላ ላይ በመንቀሳቀሱ ባለሙያዎች አገልግሎት ይሰጣሉ።በዚህ አጠቃላይ በጤና ኬላ ደረጃም ከላብራቶሪ በስተቀር የተለያዩ የጤና አገልግሎቶች በፍኖተ ካርታው እንደተካተቱም ተደርጓል ብሏል። በዚሁ ፍኖተ ካርታ መስረት በሀገር አቀፍ ደረጃ በ14 ወረዳዎች የተጀመረ ሲሆን በቤኒሻጉል ጉሙዝ ክልል መንግሰት በባምባሲ ወረዳ መንደር 43 ጤና ኬላ በፓይለት የተጀመረ ስለሆነ ለፕሮግራሙ መሳካት የሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት የበኩላቸዉን ድርሻ መወጣ እንዳለባቸዉ አቶ ክብሩ ጥሪ አቀርበዋል፡፡