Image

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

Benishangul Gumuz Regional State Health Bureau

የ2015 ዓ.ም የዕቅድ ዉይይት

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ የማኔጅመንት አባላት እና ፈፃሚዎች በተገኘበት የ2015 ዓ.ም የዕቅድ ዝግጅት ላይ ዉይይት ተደርጓል ። በጤናው ዘርፍ በ2015 ዓ.ም የታቀዱ ዕቅዶችን ወደ ትግበራ ከመገባቱ በፊት የሁሉም ፈፃሚዎች ግብዓት በማካተት ወጥ እና የተናበበ ለማድረግ ታስቦ የዉይይት መድረኩ መዘጋጀቱን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ ፍቃዱ ረጋሳ ገልፀዋል ። ዕቅድን በተናበበ መልኩ የፈፃሚዎችን ግብዓት አካቶ ማቀድ በበጀት አመቱ የተሻሉ ሥራዎችን በመስራት የህብረተሰቡን የጤና ችግሮች ለመቅረፍ እንደሚረዳ የቢሮ ሀላፊው ተናግሯል ። የ2015 ዓ.ም የታቀደው የሥራ ዕቅድ በቢሮ ማኔጅመንት አባላትና ፈፃሚዎች ዉይይት ተደርጎ የዳበረው ዕቅድ ወደ ዞኖች፣ ከተማ አስተዳደሮች እና ወረዳዎች በማዉረድ እስከ ፈፃሚ ተናቦ ስለመታቀዱ ክትትልና ድጋፍ እንደሚሰጥም አቶ ፍቃዱ አስረድተዋል ። በ2015 ዓ.ም በተደረገው የዕቅድ ዝግጅት ግምገማ ላይ የተገኙ ፈፃሚዎች በበኩላቸው በበጀት አመቱ የታቀዱ ዕቅዶች ላይ በጋራ መወያየት ከታችኛው መዋቅር ጋር የማጣጣም ሥራዎች መታሰባቸዉ ከክልል እስከ ወረዳ እየተናበቡ ሥራዎች ለመስራት እንደሚያግዝ ገልፀዋል ። በተቀመጠው ዕቅድ መሠረት ዉጤታማ የሆኑ ሥራዎች ለመሥራት የአመራር ቁርጠኝነት፣ የግብዓት አቅርቦት ፣ ለሥራ ማስፈፀሚያ የሚሆን የበጀት እና ምቹ የሥራ አከባቢዎችን የመፍጠር ጉዳይ ታሳቢ መደረግ እንዳለበት ጠይቀዋል ። የ2015 ዓ.ም የታቀደው ዕቅድ የጤና ሚ/ር ዕቅድ ፣ የክልሉ መሪ ዕቅድና የቢሮው የ2014 ዓ.ም በተደረገው የሥራ አፈጻጸም የተለዩ ተግዳሮቶች መነሻ በማድረግ የታቀደ መሆኑ ከመድረኩ ለማወቅ ተችሏል ። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ