Image

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

Benishangul Gumuz Regional State Health Bureau

የእናቶች ጤና

በለጋ ዕድሜ ማርገዝና ያለ ዕድሜ የሚፈፀም ጋብቻ ሴት ልጆችን ለዘርፈ ብዙ ችግሮች ሰለባ እንደሚያደርግ ተጠቆመ፡፡ (አሶሳ፣ ሰኔ 27/2014 ዓ.ም) የክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ በለጋ ዕድሜ ማርገዝና ያለዕድሜ ጋብቻ በሴቶች ላይ በሚያደርሱት አሉታዊ ተጽዕኖዎች ዙሪያ ከመንጌ ወረዳ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ምክክር አድርጓል፡፡ በውይይት መድረኩ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ የወጣቶች ስነ-ተዋልዶ ጤና ኦፊሰር ሲስተር ፀጋነሽ በየነ እንዳሉት በለጋ ዕድሜ ማርገዝና ያለ ዕድሜ የሚፈፀም ጋብቻ የሴት ልጆችን ለውስብስብ አካላዊ፣ ማህበራዊ፣ ስነ-ልቦናዊና ለተያያዥ ችግሮች ሰለባ እንዲሆኑ እንደሚያደርግ ገልፀዋል፡፡ በክልሉ በለጋ ዕድሜ ማርገዝና ያለ ዕድሜ የሚፈፀም ጋብቻ 23 በመቶ ላይ መድረሱን የጠቆሙት ሲስተር ፀጋነሽ ይህም የሴት ልጆች ከራሳቸው አልፈው ለሀገረ ከሚያበረክቱት አስተዋፅኦ አሉታዊ ተፅዕኖ የሚያሳርፍ ነው ብለዋል፡፡ ችግሩን ለመከላከል ሁሉም ዜጎች የሴት ልጆች በለጋ ዕድሜ እንዳያረግዙና ያለዕድሜ ጋብቻ እንዳይፈፅሙ ባለድርሻ አካላት በኃላፊነት እንዲሰሩም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የሚደረገው ግንዛቤ የመፍጠር ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል፡፡ የመንጌ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ነጅመዲን ሽኩረላ በበኩላቸው በወረዳው የሴት ልጆች በለጋ ዕድሜ እንዳያረግዙና ያለ ዕድሜ ጋብቻ እንደይፈፅሙ በሰራነው የግንዛቤ የመፍጠር ስራ በወረዳው የጎላ ችግር አለመኖሩን ጠቁመዋል፡፡ የምክክር መድረኩ ተሳታፊዎች እንደሚሉት የሴት ልጆች በለጋ ዕድሜ እንዳያረግዙና ያለ ዕድሜ ጋብቻ እንደይፈፅሙ የበኩላችንን ኃላፊነት እንወጣለን ብለዋል፡፡ የክልሉ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገበው