Image

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

Benishangul Gumuz Regional State Health Bureau

HIV

(መጋቢት 14/07/2014 ዓ.ም) ቫይረሱ በደማቸው ያሉ ወገኖችን ማግለልና መድሎ ለመከላከል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ተገለጸ፡፡ የንቅናቄ መድረኩ በባምባሲ ከተማ የተካሄደ ሲሆን በዚሁ መድረክ ላይ ቫይረሱ በደማቸው ያሉ ወገኖችን ማግለልና መድሎን አስመልክቶ ውይይት ተካሂድዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት የበሽታው ስርጭት እለት ተእለት እየጨመረ በመምጣቱ ማህበረሰቡ ላይ የሚያደርሰውን ተጽእኖ ለመቀነስ የማህበረሰብ ንቅናቄ ማካሄድ አስፈላጊ በመሆኑ ይህ መድረክ ተዘጋጅቷል፡፡ የክልሉ ጤና ጥበቃ ም/ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ አብዱልፈታ አብደራሂም የንቅናቄ መድረኩን ሲያስጀምሩ እንደተናገሩት በአሁኑ ሰዓት ለበሽታው እየተሰጠ ያለው ትኩረት እያነሰ በመምጣቱ ቫይረሱ በደማቸው ያሉ ወገኖች ላይ የሚደርሰው ተጽዕኖም በዛው ልክ እየጨመረ መምጣቱ እንዲሁም አዲስ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥርም እየጨመረ መሆኑን ገልጸው ተጽእኖውን ለመቀነስ እያንዳንዳችን የሚቻለንን ድርሻ መወጣት እንዳለብን በአጽንዖት ገልጸዋል፡፡ በክልሉ ጤና ቢሮ የማይታይ መጠን= የተገታ መተላለፍ(ዩ=ዩ) አስተባባሪ አቶ ይበልጣል ሙለታ በበኩላቸው የቫይረሱን ስርጭት መጠን ለመቀነስ ቫይረሱ በደማቸው ያሉ ወገኖች መድሀኒታቸውን በአግባቡ በመውሰድ የቫይረስ መጠናቸውን ወደማይታይ መጠንና የተገታ መተላለፍ ደረጃ ማድረስ አለባቸው ብለዋል፡፡ በተጨማሪም የምርመራ አገልግሎትን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ይህም የቫይረሱን ስርጭት ለመቀነስ ይረዳል ብለዋል፡፡ በውይይቱ መድረክ ላይ የተገኙት ሴተኛ አዳሪዎች፤ቫይረሱ በደማቸው ያሉ ወገኖች ጥምረት፤ ማህበራት፤ የጤና ኤክስቴንሽን አስተባባሪዎች፤የጤና ባለሙያዎች፤ እንዲሁም ባለድርሻ አካላት በውይይቱ ላይ የተገኙ ሲሆን ቫይረሱ በደማቸው ያሉ ወገኖችን ማግለል እና መድሎ ለማቀረት እንዲሁም የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡ የቤ/ጉ/ክለል መንግሰት ጤና ቢሮ