Image

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

Benishangul Gumuz Regional State Health Bureau

about rota vairus

በክልሉ በአሶሳ ዞን የተከሰተውን የሮታ ቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከልና ለመቆጣጠር በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ ገለጸ። በቫይረሱ እስካሁን ድረስ 549 በላይ የሚሆኑ ህጻናት መያዛቸውን ቢሮው አስታውቋል። የክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ የህብረተሰብ ጤና አደጋዎች አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ተወካይ አቶ ፍቃዱ አያሌው እንዳሉት የተቀማጥ በሽታ ሮታ በሚባል ቫይረስ አማካኝነት በየዓመቱ ከ5 ዓመት በታች በሆኑ ህጻናት ላይ እንደሚከሰት ገልጸዋል ። በ2005 ዓም ጀምሮ መሰል ቫይረስ የተለየ ቢሆኑም በ2009 በተደረገው ጥናት ሮታ ቫይረስ መሆኑን የታወቀ ሲሆን በንክኪ አማካኝነት በከፍተኛ ሁኔታ ከሰው ወደ ሰው እንደሚተላለፍ አቶ ፍቃዱ ገልጸዋል። ቫይረሱ በክልሉ በኩርሙክ ወረዳ በአብዛኛው የሚከሰተው ሲሆን አሁን ላይ በአሶሳ ከተማና በሸርቆሌ ወረዳዎች መከሰቱን ነው የተናገሩት። በሽታውን ለመከላከል የክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ የሀይማኖት አባቶች፣የሀገር ሽማግሎዎች፣የጤና ባለሙያዎች እንዲሁም የልማት ቡድን መሪዎችን በመጠቀም ለህብረተሰቡ የግንዛቤ ፈጠራ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑንና በጤና ተቋማት አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን የማሟላት ስራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አቶ ፍቃዱ አያያዘው ገልጸዋል። ውሃ መሰል ተቀማጥ፣ ትውከትና ትኩሳት የበሽታዎቹ ዋነኛ ምልክቶቹ መሆናቸው ጠቁመው ንጽህና መጠበቅ ፣ውሃን አፈልቶ እና አቀዝቅዞ መጠቀም በሽታውን ለመከላከልም እንደሚረዳ ተገልጸዋል። መላው ህብረተሰቡና ባለድርሻ አካላትም የተከሰተውን የሮታ ቫይረስ ለመከላከል የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ቢሮ ጥሪውን አስተላልፈዋል። እስካሁን ባለው ሂደት በኩርሙክ ወረዳ፣ በአሶሳ ከተማ እንዲሁም በሸርቆሌ ወረዳዎች በርካታ ህጻናት መያዛቸውን የታወቀ ሲሆን በተደረገው ህክምና ሁሉም ከበሽታው ማገገማቸውን ተገልጸዋል።