Image

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

Benishangul Gumuz Regional State Health Bureau

የበተሰብ ጤና ቡደን ሥራዎች ዉጤታማ በማድረግ የማህበረሰቡን የጤና ችግሮች ለመቅረፍ ወሳኝ ነዉ ተባለ

የበተሰብ ጤና ቡደን ሥራዎች ዉጤታማ በማድረግ የማህበረሰቡን የጤና ችግሮች ለመቅረፍ ሁሉም ባለድርሻ አካላ በበተሰብ የጤና ቡድን ላይ ያተኮረ የንቅናቄ መድረክ ተካህዷል፡፡ በቤኒሻጉል ጉሙዝ ክልል መንግሰት የበተሰብ የጤና ቡድን ፕሮግራም ከሚተገበርባቸዉ ከተማዎች አንዱ የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ነዉ። ይህ ፕሮግራም ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ በአሶሳ ከተማ በአድስ መልክ ተደራጅቶ ወደ ስራ የገባ ቢሆንም ፕረግራሙ የህብረተሰቡን የጤና ችግሮች ቀድሞ በመለየት የህብረተሰቡን የጤና ችግሮች ለመቅረፍ የተከናወኑ ተግባራ አመርቂ አለመሆናቸዉን በተለያዩ ጊዜያት በተደረጉ የመስክ ጉብኝቶችና የስራ ግምገማዎች ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡ እነዚህን ችግሮች በመቅረፍ እና ፕሮግራሙ በተፈለግ መልኩ ወደ ስራ በመግባት የህብረተሰቡን የጤና ችግሮች መቅርፍ እንዲችል ለማድረግ በፕሮግራሙ ላይ የሁሉም ባለድርሻ አካላት በተለይም የአመራር አካላት ግንዛቤ ማዳበር አስፈላጊ በመሆኑ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተዘጋጅቷል፡፡ በቤ/ጉ/ክ/መ/ጤና ቢሮ የኦፕረሽን ዘርፍ ምክትል የቢሮ ሀላፊ አቶ ወልተጅ በጋሎ የንቅናቄ መድረኩን ሲከፊቱ እንዳሉት የበተሰብ የጤና ቡድን የማህበረሰበን የጤና ሁኔታዎች በመለየት የተለዩ የጤና ችግሮችን መነሻ በማድረግ ቤት ለቤት በመሄድ አስፈላጊዉን የጤና አገልግሎቶች ደረጃ በደረጃ ተደራሽ በማድረግ የህብረተሰቡን የጤና ችግሮች የመቅረፍ አለማ መስረት አድረጎ የተደራጀ መሆኑን ነዉ፡፡ ፕሮግራሙ ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች፤የተለያዩ አካላዊና ስነልቦናዊ የጤና ሁኔታዎች ፤የትራፊክ አደጋዎች፤ረዳት የለላቸዉ በቤት ዉስጥ በተለያዩ ህመም የሚሰቃዩና ተስፋ የቆረጡ ወገኖችን ለመርዳት በከተማዉ የተጀመረ ቢሆንም በተፈለገ መልኩ ወደ ስራ ከማስገባት አንጸር የባለድርሻ አካላት እና የአመራር አከላት እገዛ የተፈለገዉን ያህል ባለመሆኑ ፕረግራሙ ዉጤት እያስመዘገበ እንዳልሆነ አቶ ወልተጅ ገልጸዋል፡፡ አቶ ወልተጅ አክለዉም የበተሰብ የጤና ቡድን ስራ በጤና መዋቅሮች ብቻ ዉጤታማ የሚሆን ባለመሆኑ የሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት ለፕሮግራሙ መሳካት የበኩላቸዉን ድርሻ መወጣት እንዳለባቸዉ ጥሪ አቀርበዉ የክልሉ ጤና ቢሮም ከከተማ ጤና መምሪያ ጋር በመሆን አስፈላጊዉን ሁል እገዛ በማድረግ ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ላይ የነበሩ ባለድርሻ አካላት እና የከተማዉ አመራር አካላት በበኩላቸዉ የግንዛቤ መድረኩ መዘጋጀቱ በፕሮግራሙ ላይ የጠራ ግንዛቤ እንዲኖራቸዉ እንዳገዛቸዉ ገልጸዉ ለፕሮግራሙ መሳካት አስፈላጊዉን ሁል ለማድረግና የህብረተሰቡን የጤና ችግር ለመቅረፍ እንሰራለን ብለዋል የቤ/ጉ/ክ/መ/ጤና ቢሮ የበተሰብ ጤና ቡደን ሥራዎች ዉጤታማ በማድረግ የማህበረሰቡን የጤና ችግሮች ለመቅረፍ ሁሉም ባለድርሻ አካላ በበተሰብ የጤና ቡድን ላይ ያተኮረ የንቅናቄ መድረክ ተካህዷል፡፡ በቤኒሻጉል ጉሙዝ ክልል መንግሰት የበተሰብ የጤና ቡድን ፕሮግራም ከሚተገበርባቸዉ ከተማዎች አንዱ የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ነዉ። ይህ ፕሮግራም ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ በአሶሳ ከተማ በአድስ መልክ ተደራጅቶ ወደ ስራ የገባ ቢሆንም ፕረግራሙ የህብረተሰቡን የጤና ችግሮች ቀድሞ በመለየት የህብረተሰቡን የጤና ችግሮች ለመቅረፍ የተከናወኑ ተግባራ አመርቂ አለመሆናቸዉን በተለያዩ ጊዜያት በተደረጉ የመስክ ጉብኝቶችና የስራ ግምገማዎች ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡ እነዚህን ችግሮች በመቅረፍ እና ፕሮግራሙ በተፈለግ መልኩ ወደ ስራ በመግባት የህብረተሰቡን የጤና ችግሮች መቅርፍ እንዲችል ለማድረግ በፕሮግራሙ ላይ የሁሉም ባለድርሻ አካላት በተለይም የአመራር አካላት ግንዛቤ ማዳበር አስፈላጊ በመሆኑ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተዘጋጅቷል፡፡ በቤ/ጉ/ክ/መ/ጤና ቢሮ የኦፕረሽን ዘርፍ ምክትል የቢሮ ሀላፊ አቶ ወልተጅ በጋሎ የንቅናቄ መድረኩን ሲከፊቱ እንዳሉት የበተሰብ የጤና ቡድን የማህበረሰበን የጤና ሁኔታዎች በመለየት የተለዩ የጤና ችግሮችን መነሻ በማድረግ ቤት ለቤት በመሄድ አስፈላጊዉን የጤና አገልግሎቶች ደረጃ በደረጃ ተደራሽ በማድረግ የህብረተሰቡን የጤና ችግሮች የመቅረፍ አለማ መስረት አድረጎ የተደራጀ መሆኑን ነዉ፡፡ ፕሮግራሙ ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች፤የተለያዩ አካላዊና ስነልቦናዊ የጤና ሁኔታዎች ፤የትራፊክ አደጋዎች፤ረዳት የለላቸዉ በቤት ዉስጥ በተለያዩ ህመም የሚሰቃዩና ተስፋ የቆረጡ ወገኖችን ለመርዳት በከተማዉ የተጀመረ ቢሆንም በተፈለገ መልኩ ወደ ስራ ከማስገባት አንጸር የባለድርሻ አካላት እና የአመራር አከላት እገዛ የተፈለገዉን ያህል ባለመሆኑ ፕረግራሙ ዉጤት እያስመዘገበ እንዳልሆነ አቶ ወልተጅ ገልጸዋል፡፡ አቶ ወልተጅ አክለዉም የበተሰብ የጤና ቡድን ስራ በጤና መዋቅሮች ብቻ ዉጤታማ የሚሆን ባለመሆኑ የሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት ለፕሮግራሙ መሳካት የበኩላቸዉን ድርሻ መወጣት እንዳለባቸዉ ጥሪ አቀርበዉ የክልሉ ጤና ቢሮም ከከተማ ጤና መምሪያ ጋር በመሆን አስፈላጊዉን ሁል እገዛ በማድረግ ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ላይ የነበሩ ባለድርሻ አካላት እና የከተማዉ አመራር አካላት በበኩላቸዉ የግንዛቤ መድረኩ መዘጋጀቱ በፕሮግራሙ ላይ የጠራ ግንዛቤ እንዲኖራቸዉ እንዳገዛቸዉ ገልጸዉ ለፕሮግራሙ መሳካት አስፈላጊዉን ሁል ለማድረግና የህብረተሰቡን የጤና ችግር ለመቅረፍ እንሰራለን ብለዋል የቤ/ጉ/ክ/መ/ጤና ቢሮ