Image

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

Benishangul Gumuz Regional State Health Bureau

ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የተደረገ ድጋፍ

ለሀገር መከላከያ ሰራዊት የሚያደርጉትን እገዛ ዐጠናክሮ እንደሚቀጥሉ የቤኒሻጉል ጉሙዝ ክልል ሴት የመንግስት ሰራተኞች ገለጹ ፡፡ የቤ/ጉ/ክ/መ/ጤ/ቢሮ የሴቶች ፎረም ግምታቸዉ ከ25000.00 ብር በላይ የሆኑ የምግብ ቁሳቁሶችናና አልበሳትን ለሀገር መከላከያ እና በተለያዩ ምክንያት ተፈናቅለዉ በመጠልያ ጣቢያዎች ለሚገኙ ወገኖች አበረከቱ፡፡ የቤኒሻጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ የሴቶች ፎረም ተወካይ ወ/ሪት ወሰነ እሸቱ ስጦታዉን ባበረከቱበት ወቅት እንዳሉት የቤ/ጉ/ክ/መ/ጤና ቢሮ የሴቶች ፎረም ለሀገር መከላከያ ሰራዊትና በተለያዩ ምክንያት ከቀያቸዉ ለተፈላቀሉ ወገኖች ቀደም የተለያዩ እገዛዎችን ሲያደርግ እንደነበረ ገልጸዉ አሁንም የፎረሙ አባላት ከተለያዩ ወገኖች ያሰባሰቡትን እና ከፎረማቸዉ በማዋጥት ለማበርከት መቻላቸዉንና ይህ የተጀመረዉ እገዛ አጠናክሮ እንዲሚቀጥሉና ከመከላከያ ጎን ለመቆም ዝግጁ መሆናቸዉን ተናግረዋል፡፡ የቤ/ጉ/ክ/ሴ/ወ/ህጻናት ጉዳዮች ቢሮ ተወካይ ወ/ሮ መታሰቢያ ገሰሰ በክልሉ ጤና ቢሮ የሴቶች ፎረም የተደረገዉን እርዳታ በተረከቡበት ወቅት እንዳሉት የቤ/ጉ/ክ/መ/ ጤና ቢሮ የሴቶች ፎረም ላደረገዉ እርዳት ምስጋናቸዉን አቀርበዉ ችግሩ በዘለቄታዊነት እስክፈታ ድረስ ይህ የተጀመረዉ እገዛ አጠተናክሮ መቀጠል እንዳለበት ጠይቀዋል፡፡ የቤ/ጉ/ክ/መ/ጤና ቢሮ