Image

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

Benishangul Gumuz Regional State Health Bureau

covide 19 vaccine update

በ/ቤ/ጉ/ክ/መ/ጤና ቢሮ የተጀመረው የኮቪድ19 ክትባት ዘመቻ ስከታማ እንደነበረ ተገለፀ። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ የእናቶች ፣ ወጣቶች፣የህጻናት እና የስርዓተ ምግብ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አብዱልሚኒየም አልበሽር ዘመቻዉ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ የዘመቻዉ ሂደት በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ በመሆኑን ገልፀዉ ባለፉት 3 ቀናት ውስጥ 18,0073 ሰዎችክትባቱን መወሰዳቸውን ገልፀዋል ። ክትባቱ በክልሉ አሶሳ ዞን ሁሉም ወረዳዎች ሸርቆሌን ወረዳን ሳይጨምር፤ ከመተከል ዞን ጉባ እና ድባጢ ወረዳዎችን ሳይጨምር ፣ በማኦ እና ኮሞ ልዩ ወረዳ እየተሰጠ የሚገኝ ሲሆን ካማሽ ዞን ሁሉም ወረዳዎች በጸጥታ ችግር ምክንያት እየተሰጠ እንዳልሆነ አቶ አብዱልሙኒየም ተናግረዋል ፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የሸርቆሌ ወረዳ የፀጥታ ሁኔታም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ በመምጣቱ የፊታችን አርብ ጀምሮ ክትባቱ መሰጠት እንደሚጀምር ገልጸው ። በሁሉም ወረዳዎች የህብረተሰቡ የመከተብ ፍላጎት እየጨመረ መሆኑን የገለፁት አቶ አብዱልሙኒየም ከግብአት ጋር በተያያዘ የሚስተዋሉ ማነቆዎችን ለመፍታትና ክትባቱ በተያዘለት የጊዜ ሠሌዳ እንዲጠናቀቅ ቢሮ እየሠራ በመሆኑ የሚመለከታቸዉ አካላትም የበኩላቸዉን ድርሻ መወጣት እንዳለባቸዉ ጥሪ አቀርበዋል። አሁንም የሚያስፈልጉ ግብአቶች ሙሉ ለሙሉ ያልገቡ ቢሆንም ያለውን ግብአት በመጠቀም በባለፉት 3 ቀናት የክትባት ሽፋኑ 52 በመቶ መድረስ መቻሉ ጥሩ ጅምር ነዉ ብለዋል። ከክትባት ግብዓት በተጨማሪ ለክትባት ዘመቻ እንቅፋት እየሆነ ያለዉ በከተማዉ የነዳጅና ቤንዚን አቀርቦት አለመኖር እና የሚመለከታቸዉ አካላት ለዘመቻዉ ትኩረት አለመስጠት በመሆኑ የሚመለከታቸዉ አካላት ትኩረት እንደሚያሻ ተናግረዋል። አሁን ያለው የህብረተሰቡ የመከተብ ሁኔታ ጥሩ ቢሆንም የኮሮና ቫይረስ በሽታ ስርጭት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እየመጣ ማህበረሰቡ ክትባት በመከተብ እራሳቸዉን፣ ቤተሰባቸውን እና ማህበረሰብን ከዚህ አስከፊ በሽታ መከላከል እንዳለበት አሳስበዋል። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ ለበለጠ መረጃ 6016 ነፃ የስልክ መስመር ይጠቀሙ