Image

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

Benishangul Gumuz Regional State Health Bureau

covide 19 daily update

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሰት በባለፉት 24 ሰዓት ለ108 ሰዎች በተደረገው የላብራቶሪ ምርመራ 3 ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ የተገኘ ስሆን 1 ሰዉ ከበሽታዉ አገግሟል፡፡ እስከዛሬ የተደረገ አጠቃላይ የላብራቶሪ ምርመራ 56,977 የደረሰ ሲሆን 4,042 ሰዎች ደግሞ እስከአሁን በቫይረሱ ተይዘዋል። በሌላ በኩል 3,901 ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና እስከአሁን ማገገም መቻላቸውን መረጃው ያመላክታል።አሁን ላይ 103 ሰዎች ህክምናቸውን በቤትና በህክምና ተቋማት በመከታተል ላይ የሚገኙ ሲሆን በዛሬዉ ዕለት የ1 ሰዉ ህይወት በኮሮና ሲሞት በአጠቃላይ በክልሉ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥርም 37 ደርሰዋል። ህብረተሰቡ የበሽታዉን ስርጭትና በበሽታዉ የሚሞቱ ሰዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ መጨመሩን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት እየተሰጠ ያለዉን ክትባት መዉሰድ እንዳለበት እናሳስባለን፡፡ ለበለጠ መረጃ በነጻ ስልክ ቁጥር 6016 ይደውሉ የቤኒሻጉል ጉሙዝ መንግስት ክልሉ ጤና ቢሮ