Image

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

Benishangul Gumuz Regional State Health Bureau

የፖሊዮ ዘመቻ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከጥቅምት 12 እስከ 15/2014 ዓ.ም የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ እንደሚካሄድ የክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ አስታወቀ። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ዕድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች ለሆኑ ህጻናት ከጥቅምት 12 እስከ 15/2014 ዓ.ም የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ እንደሚካሄድ የክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ አስታወቀ፡፡ የቢሮው የፕሮግራም ዘርፍ ምክትል ኃላፊ አብዱልፈታ አብዱራሂም ዘመቻውን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፣ የፖሊዮ በሽታ ህጻናትን ለህመም፣ ሞትና ለአካል ጉዳት የሚዳርግ ነው፡፡ በሃገር ደረጃ የፖሊዮ በሽታን ለማጥፋት በተደረገው ጥረት እ.ኤ.አ በ2017 ሃገሪቱ ከፖሊዮ ቫይረስ ነጻ ሆና እንደነበር የገለጹት አቶ አብዱልፈታ፣ በተለያዩ ጎሮቤት ሃገራት በተወሰደ ናሙና የፖሊዮ በሽታ በመስተዋሉ ክትባቱን መስጠት አስፈላጊ ሆኗል ብለዋል፡፡ ምክትል ኃላፊው አክለውም፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከ5 ዓመት በታች ለሆኑ ህጻናት ከጥቅምት 12 እስከ 15/2014 ዓ.ም የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ እንደሚካሄድ አስታውቀዋል፡፡ የአሶሳ ከተማን ጨምሮ በአሶሳ ዞን ሁሉም ወረዳዎችና በማኦና ኮሞ ልዩ ወረዳ እንዲሁም በስደተኛ ካምፖች ክትባቱን ለመስጠት የሚያስችል አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን አቶ አብዱልፈታ ተናግረዋል፡፡ በዘመቻውም በተጠቀሱት አካባቢዎች ከዚህ በፊት ቢከተቡም ባይከተቡም ዕድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ከ134 ሺህ በላይ ህጻናት እንደሚከተቡም አስረድተዋል፡፡ የክትባት ዘመቻው ቤት ለቤት እንደሚሰጥ የገለጹት አቶ አብዱልፈታ፣ ወላጆች በዘመቻው ቀናት በቤታቸው በመቆዬት ህጻናትን በመስከተብ ግዴታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በጸጥታ ችግር ምክንያት ክትባቱ አሁን በማይሰጥባቸው አካባቢዎች ደግሞ በቀጣይ በዘመቻ መልክ እንደሚሰጥም ነው አቶ አብዱልፈታ በመግለጫው የጠቆሙት፡፡ ለዘመቻው መሳካት የኃይማኖት አባቶች፣ የሃገር ሽማግሎዎች፣ የጎሳ መሪዎች፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉም ቢሮው ጥሪ ማቅረቡን የክልሉ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት መረጃ የያመላክታል።