Image

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ

Benishangul Gumuz Regional State Health Bureau

እንደ ሀገር በመጪው 2030 G.C ከኤች አይ ቪ ኤድስ ነጻ የሆነ ትውልድ የመፍጠር ራዕይን በክልላችን ዕውን ለማድረግ የሚደረገው ጥረትን ባለድርሻ አካላት ማገዝ እንዳለባቸው ተገለጸ።

ኤች አይ ቪ ኤድስ ማህበረሰቡ ላይ የሚያደርሰውን ተጽዕኖ ለመቀነስ ለቫይረሱ ይበልጥ ተገላጭ ከሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችና ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ውይይት በክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ አዘጋጀነት በባምባሲ ከተማ ተካሂዷል። የክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ ሀላፊ ተወካይ አቶ ኑረዲን አሰይድ ውይይቱን ባስጀመሩበት ወቅት እንዳሉት አሁን አሁን በክልሉ ለቫይረሱ የሚሰጠው ትኩረት ዝቅተኛ በመሆኑ ኤች አይ ቪ ኤድስ ማህበረሰቡ ላይ የሚያደርሰው ተጽዕኖ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል። ለኤች አይ ቪ ኤድስ ይበልጥ ተገላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ ቢሮው በትኩረት እየሰራ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ኑረዲን በተለይ በመጪው 2030 GC እንደ ሀገር ከቫይረሱ ነጻ የሆነ ትውልድን ለመጠር የተያዘው ራዕይን በክልሉ ለማሳካት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ከጤናው ዘርፍ ጎን በመቆም ሊያግዝ እንደሚገባ አስገንዝበዋል ። በክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ የግሎባል ፈንድ ፕሮጀክት ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ግርማው ነመራ በበኩላቸው የቫይረሱን ስርጭት ለመቀነስ ተከታታይነት ያለው የባህሪ ለውጥ ትግባቦት ስራውን የማጠናከር ፣ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችና ጾታዊ ጥቃት እንዲቀነሱ የማድረግ፣የኮንዶም አጠቃቀምን ማጎልበትን ቀዳሚ ተግባር ተደርጎ እየተሰራ ነው ብልዋል። ስለሆነም ተገላጭ ተኮር አገልግሎት የሚሰጡ የህክምና ተቋማትን በክልሉ ማጠናከር፣ የሴተኛ አዳሪ ማቆያ ማዕከላትን በክልሉ እንዲኖር ማድረግ ፣የኤች አይ ቪ ኤድስ አገልግሎት ከለሎች የጤና ስራዎች ጋር ማቀናጀትና ቁልፍ የሆኑ ተቋማት ጋር በቅርበት መስራት በቀጣይ ትኩረት በመስጠት ሊሰሩ የሚገባ ጉዳዮች መሆናቸውን አቶ ግርማው ባቀረቡት ጽሁፍ አመልክቷል ። በመድረኩ ላይ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች፣ጾታዊ ጥቃትና በጤና ላይ የሚያደርሰውን ተጽዕኖ በሚመለከትና ተያያዥ ጉዳዮችን የሚዳስስ ጽሁፍ ቀርቦ በተሳታፊዎች ሰፊ ውይይት ተደርጓል ። ሴተኛ አዳሪዎች፣የህግ ታራሚዎች፣አደንዛዥ ዕጽ ተጠቃሚዎች እንዲሁም የረጅም ርቀት አሽከርካሪዎች ለቫይረሱ ይበልጥ ተገላጭ መሆናቸው በመድረኩ ተገልጸዋል። በውውይት መድረኩ ላይ የፍትህ ተቋማት፣ ከሴቶች ወጣቶችና ህጻናት ቢሮ ፣ከፖሊስ፣ማረሚያ ቤቶች፣ ከሆቴሎች፣ከሴተኛ አዳሪ አመቻቾች እንዲሁም ለሎች ቁልፍ የሆኑ ባለድርሻ አካልት የተሳተፉ ሲሆን በሰጡት አስተያየት ኤች አይ ቪ ኤድስ ማህበረሰቡ ላይ የሚደርሰው ተጽዕኖ ከፍተኛ መሆኑን መገንዝብ መቻላቸውን ገልጸው ቫይረሱን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረትን ለማገዝ የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡ ተናግረዋል።